ክንድህን አውሰኝ አያ,,,
የምትረታበትን ፍልምያ፣
የትውልድህን ማቆያ፣
ያገር ፍቅርህን መለያ፣
ድምጽህን ተውልኝ ወገን,,,,
የሃቅ ፋና ወጊዉን፣
ህብር ተስፋ ናፋቂውን፣
ድል ነጋሪ ያን ዜናውን፣
እውነት ብሎ የቀረውን፣
ወያኔ ላይ ያበረውን፣
ኢሳት ንጋት አብሳሪውን ፣
ቃልህን ተውልኝ ጓዴ,,,,
ያን ምክርህን ፣ያንን ዘዴ፣
ስንቅ ይሆነኛል ለሆዴ፣
አቅፎ ያነሳኛል ከዳዴ፣
ካላማህ ነው መዋደዴ፣
ኢትዬጵያዊ ነው ውልዴ፣
እኮ! ልብህን ሸልመኝ
አያ!
ያገር ፍቅሬን መለያ፣
ይመጥን ይሆን ክፍያ፣
ባዋጣልህ፥ባደባባይ፣በገበያ፣
ላንተ ትግል,,,,ላንተ ፍልምያ፣
ከኔው ጓዳ,,,,ከኔው
ጒያ!!
ይመጥን ይሆን አያ,,,,!!
ኢሳት
የውለታህን ክፍያ፣
ለትግል
ሂደትህ መቆያ፣
ለአላማህ፣ለጽናትህ፣ለዚህ ሙያ፣
ለሰው በላው፣ለወያኔው፣ወድቆ ማያ፣
ይመጥን
ይሆን ክፍያ !
,,,,ባወጣልህ ከእኔ
ጒያ፣፣
ከሹሜ ወርቄ
ኖርዌይ
Excellent, I am totally agree with you. It will be our duty to support Esat and we will continue doing it until the end of this fascist woyane regime.
ReplyDelete