Monday, February 18, 2013

ውሸትና ስንቅ




ከሹሜ ወርቁ

            ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በዘመኑ ታላቅ የነበረው የሮማውያን ኢምፓየር መንኮታኮት በጀመረበት 17ኛው ... መገባደጃ ላይ፡ በዓለማችን፡ በተለይም በአውሮፓ አንድ ታላቅ የባህል ንቅናቄ (Cultural Revolution) ተነሣ ንቅናቄው በዕጅጉ ምናባዊነት የበዛበት የአኗኗር ዘይቤዎች የተጋነኑበት፤ ያለ ቅጥ መሽሞንሞን የበዛበት እንዲሁም መዋሸትና ማስመሰል የተፈቀደበት የፍልስፍና ዘመን ነበር።

            ይሄንን ጊዜ ነበር የፈረንሣውያን የዕውነታዊ (realistic) ንቅናቄ አራማጆችን አስቆጥቶ ለሌላ ንቅናቄ ያስነሣው ንቅናቄው እየተኖረ ካለው የገሃዱ ዓለም ዕውነታ ጋር ሲነጻጸር፤ ያልነበረ የሌለና የማይኖር ሀሰት ነውና እውነትን ሳንሸቅጥ ሳናሽሞነሙንና ሳናጋንን እንናገር፤ እንስማ እንይና እንኑር ብሎ ተነሣ .... በዕርግጥም ተወዳጅና የተዋጣለት እንቅስቃሴ ነበር። ... እጅግ ግሩም !

            ... ሰጎን ትልቅ ናት። ደግሞ አስገራሚ የሆነ የሩጫ ክህሎት የተቸራት። ታዲያ ይሄንን ክህሎቷን የሚያውቁ አውሬዎች በደቦ ከየአቅጣጫው ሊያድኑዋት የተመሙባት እንደሆነ ወዳ አሸዋ ትሮጣለች። አንገትዋን ብቻ አሸዋ ውስጥ ቀብራ ከሞቷ ለመታደግ የእንስሳቱን ተመራማሪዎች እንደሚሉት በእርግጥ አንገቷን መቅበሯ ከፍራሃቷ ነጻ ከመውጣቷ ባሻገር ሙሉ በሙሉ የተሸሸገችና ከሞት ያመለጠች ይመስላታል።

            ዕነታውያውኑ እንዲሁ ነው ያሉት እውነትን እንደ ሰጎን አንገታችችንንበመሰወር ከመታየት አናመልጥም። እንዳየነውና እንደሰማነው እንኖራለን ለእውነት እንቆማለን፤ ዕውነትን እናወራለን እንጂ አንሸሽም እያሉ በመነሰታቸው ነበር። ተቀባይናተወዳጅ የነበሩት በእርግጥ እውነት ነውና በጊዜው መርታቱ አይቀሬ ነው።

            ገዢ ነን የሚሉት ፓርቲዎች (ወያኔ) እያደረገ ያለው የሜዳ ድፍረትና የጓዳ ገበና ዛሬ ዛሬ ባደባባይ ፀሀይ እየሞቀው ሃገር እየዘገበው ህዝብ እያደመጠው እንደ ሰጎን አንገቱን በፓርላማ አሸዋ ውስጥ መሽጎ አላየሁም አልሰማሁም ሲሉ
አለማፈራቸው ያሳፍራል። ናዳ መጣብህ ሲሉት ተከናንቢያለሁ አለ ይሏል እንዲህ ነው።

            በአንድ በኩል ምጣኔ ሀብታችን በዚህን ያህል ተመነደገ የእገሌ ጥናት ዘገባ እያለ ፓርላማ ተቀምጦ ሲያራግብ። በሌላ በኩል ደግሞ የዓለማችን ታላላቅ የሆኑት የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችና ዘጋቢዎች በግልጽና በተጨበጠ መረጃ በተደገፈ
የሚያሳዩዋቸውን ዘገባዎች የህዝብ ጭቆናና የመብት ረገጣ ጉዳዬና እኛን አይገልጽም የተዛባና የውሸት መረጃ ነው ሲሉ አንድም የሰፊውን ህዝብ ንቀት ሲሆን ሁለትም የዘመናቸው ማብቂያ ዋዜማ ላይ መሆናቸውን ማመላከቻ መሆኑ ጥርጥር የለውም።

            በቅርቡ ሚኒስቴሩ በግልጽ እስረኛ የለኝም ሲሉ በፓርላማ ተደምጠዋል። ዕውነት ብለዋል በእርግጥም እንደ እኛ እስረኛ የለም የሃገሩን ፍትህ የሀገሩን ነጻነትና የሃገሩን ሰላም ዘልቆም የህሊናውን ነጻነት የጠበቀ በአካሉ ታስሮ ህሊናውን የፈታ ነጻ ህዝብናታጋይ እንጂ እስረኛ የለም . . . ለነገሩ ይህንን ባነጋገራቸውም ራሳቸውም ጠንቅቀው ያውቁታል። አለኝ ብሎ ከማፈር የለኝም ብሎ መድፈር ሆኖባቸው  እንጂ

           
     ነጻነታቸውን ሽተው በተባ ብዕራቸው ያነቡትን በየጎዳናው በየአደባባዩና በየሜዳው ነጻነታችን ይከበር እያሉ የጮሁትን ዜጎቹን ጠራርጎ አጉረው እስረጉረው እስረኛ የለንም እያሉ በፓርላማ ሲናፉ በዕርግጥም ያስገርማል።

            አንድ ነገር ይገርመኛል እነርሱ በፓርላማ ተቀምጠው እስረኛ የለንም በሚሉበት በዛው ሳምንት እምቢ ለነጻነታችን ብለው የወጡትን በሽዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሰብስቦ ያጎራቸውን ምን ሊላቸው ይሆን? በየሳምንቱ ከየመስጊድ
የሚያፍሳቸውን ሙስሊም ወንድሞቻችንን፤ በቅርቡ ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ የለቀማቸውን ተማሪዎች እና ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን፤ ርዕዮት አለሙን፤ እስክንድር ነጋን ኧረ ስንቱን ምን እያለ ሊጠራቸው ይሆን ? ግድ የለም ለዚህ መልስ አንሻም።

            ከጥቂት ዓሥርተ ዓመታት በፊት የሚኒስተ ገዢ (governor) ቀጥለውም የአሜሪካውያኑ ሪፐብሊካን ቫይስ ፕሬዘዳንት የነበሩት ሁበርት ሆራቶኒ በህዝብ ያልተደገፈን መንግስት አስተዳደርን ሲገልጹ ያሉት አባባል ነገሬን ይቋልኝ እንደሁ ላካፍችሁ።

                        There are not enough jails, not enough policeman, not enough courts to enforce a low not supported by the people.  

            

ድል ለሰፊው  ህዝብ !

No comments:

Post a Comment